በአዲስ አበባ በሚገኘው በማርዮት አክስክዩቲቭ አፓርታማዎች የጎልደን ድራጎን ይፋዊ መክፈቻ ስነስርዓት

በመካከለኛው ምስራቅ እና በምስራቅ አፍሪካ፣ በአለማችን የታወቁ በርካታ ተሽከርካሪዎች ግንባር ቀደም አከፋፋይ የሆነው ሰዒድ መሐመድ አልጋንዲ ሀሙስ እ.ኤ.አ መስከረም 8/2016 በማርዮት አክስክዩቲቭ አፓርታትመንቶች፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ጎልደን ድራገን አውቶቢሶችን በይፋ መርቆዋቸዋል፡፡

ሰዒድ መሐመድ አልጋንዲ እና ልጆቹ በመካከለኛው ምስራቅ እና በምስራቅ አፍሪካ ክልሎች እና በኢትዮጵያ የማህበሩ ተወካይ ጽ/ቤት የኢትዮጵያን የትራንስፖርት ስርዓት ለመደገፍ እና የከተማ እንቅስቃሴውን ለማሳለጥ የኮኔክሽን ማስፋፊያ እንቅስቃሴዎች ላይ ድጋፍ የሚያደርጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን ከፍተኛ ፍላጎት ለማርካት ሲባል በአለማችን ውስጥ በእጅጉ የታወቀ የኢንዱስትሪ ማሽነሪ እና ቁሳቁስ ጥምረቶች የንግድ ተሽከርካሪዎች እና መሳሪያዎችን በማቅረቡ ረገድ ከ50 አመታት በላይ ልምዱ አላቸው፡፡

በአዲስ አበባ ነጋ ሲቲ ሞል የሚገኙ የወኪል ጽ/ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚገኝ ከፍተኛ የስርጭት ማዕከል ጋራ ግንኙነት በመፍጠር ሽያጮችን፣ የቴክኒክ እና የመለዋወጫ አካላትን የሚደግፍ ነው፡፡ ሁሉም የአይኤስኦ 9001 እውቅና ያላቸው ናቸው፡፡

ማህበሩ በቻይና ውስጥ ካሉት 10 የአውቶብስ አምራቾች እንዲሁም 10 የአውቶብስ ብራንዶች ግምባር ቀደም የሆነውን ጎልደን ድራጎን አውቶብሶችን አስተዋውቆዋል፡፡ እስከ አሁን ድረስ አውቶብሶቹ በኢስያ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ እና  ደቡብ አሜሪካ 40 በሚጠጉ አገራቶች ውስጥ ሲላኩ የቆዩ ሲሆን ወደ አውሮፖ ገበያም በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የቅንጦት አውቶብሶች በአንድ ጊዜ 61 ተሳፋሪዎችን ማሳፈር የሚችሉ 15 ክፍት ቦታዎችን ያካተተ ነው፡፡

ኤስኤምኤጂ በግንባታው ኢንደስትሪ ከ60 አመታት በላይ ልምዱ ካላቸው ከጣና ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ጋር በመተባበር የሽያጭ በኋላ፣ የመለዋወጫ አካላት እና የቴክኒክ ድጋፍ ያቀርባል፡፡ የኤስኤምኤጂ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ግርሃም ተርነር እንዳመለከቱት ከሆነ ‹‹ለግንባታ ቁሳቁሶች እያደገ የመጣውን የህዝብ ቁጥር፣ የሀገር ውስጥ ምርት ምጣኔ፣ አገልግሎት ስር ላይ ያልዋሉ አገልግሎቶች እና መሰረተ ልማት እና የግንባታ ቁሳቁሶች ፍላጎቶች ለኢኮኖሚ መሰረቶች በትክክለኛው አቅጣጫ መሆኗን የሚያመላክት በቂ መረጃ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ ለኤስኤምኤጂ ከበርካታ አመታት በፊት ይህንን አቅም የተመለከትን ሲሆን የፈረምነው ይህ አዲሱ የንግድ ጥምረት ስምምነቶች በአፍሪካ ገበያ ውስጥ እና በተለይም ዛሬ ጎልደን ድራገንን በምናስተዋውቅበት ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለንን ስራ እንድናሳድግ ገፋፍቶናል፡፡››

ለበለጠ መረጃ -ሰዒድ መሐመድ አልጋንዲ እና ልጆቹ (ወኪል ጽ/ቤት) ጆሴፍ ቲቶ ጎዳና፣ ነጋ ሲቲ ሞል፣ 2ኛፎቅ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ ስልክ +2511155714114 ኢሜይል፡ smag@alghandi.com